Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አንዳንድ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት እያራመዱት ያለው የጥላቻ ዘመቻ ማህበረሰቡ አሁን ያለበትን ሁኔታ ያላማከለ መሆኑን ምሁራን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አንዳንድ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት እያራመዱት ያለው የጥላቻ ዘመቻ ማህበረሰቡ አሁን ያለበትን ሁኔታ ያላማከለ ነው ሲሉ የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ባለሙያዎቹ አሁን ላይ ለነጻ ሃሳብ የተዘረጋው መንገድ ተስፋ የሚሰጥ በሆነበት ወቅት የቀደመውን አካሄድ መከተሉ በምክንያታዊነት ከመጓዝ ይልቅ በጥቂቶች ጭንቅላት ማሰብን ማሳያ ነው ብለዋል።

ህዝብን ነፃ ማውጣት የሚቻለው እንደ ማህበረሰቡ በመሆን እንጂ ጫካና ውጭ ሀገራት ሆኖ አይደለም ብለዋል የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ዳንኤል አሰፋ።

በዳያስፖራው ማህበረሰብ የሚታየው የጥላቻ ዘመቻ ለህዝብም ሆነ ለሀገር የማይበጅ ነገን የማያሻግር እና አሁናዊ የግል ጥቅም የተመረከዞ መሆኑን ባለሙያዎች ተናግረዋል።

የፖለቲካ ምሁሩ አቶ ከድር ማሞ በበኩላቸው ሁልጊዜም በተመሳሳይ የትግል መስመር መሄድ ትግል አይደለም ነው ያሉት።

በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በኩል በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ዳያስፖራዎችን ባሉበት ሀገር በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ መንግስት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ አቶ አንዱዓለም በዛብህ ናቸው።

መንግስት አሁንም በጀመረው ልክ ህግ የማስከበርና የዜጎችን ህልውና የማስጠበቁን ስራ ለነገ ሳይል አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት።

በፍሬህይወት ሰፊው

Exit mobile version