Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተወያዩ።

ውይይታቸው ጄኔቫ በሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ፅህፈት ቤት የተደረገ ነው።

በውይይታቸውም በሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን፣ በቅድመ ጤና አጠባበቅ፣ በተመጣጠነ ምግብ፣ በህክምና መሳሪያዎች እና ቁሳቁስ አቅርቦት እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዙሪያ መክረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ልማት ለሚጫወተው አጋዥ ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፥ የዓለም ጤና ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

በውይይቱ በተነሱ ነጥቦች ዙሪያም ድርጅቱ ድጋፉን እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version