Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን በመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመገኘት ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጋር ችግኝ ተክለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀንበር 2 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች ተካሂዷል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቦች እና የከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስሩ በአንድ ጀምበር 2 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ላይ እተሳተፉ ዜጎች ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version