Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል የፊታችን ጳጉሜን 5 ስራ ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የተገነባው የኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል የፊታችን ጳጉሜን 5 ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን  ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።

ሆስፒታሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በአለም ምግብ ፕሮግራምና በአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተገነባ ነው።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታምሩ አሰፋ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩትም፥ ሆስፒታሉ የፊታችን ጳጉሜን 5 ስራ ይጀምራል።

በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምርም  200 አልጋ እንደሚኖረው ዶክተር ታምሩ ገልጸዋል።

Exit mobile version