አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 10 ሺህ 322 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 616 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 68 ሺህ 131 ደርሷል።
በሌላ በኩል 301 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 27 ሺህ 939 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።