Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ100 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን በዛሬው ዕለት የ100 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር ተፈራርመውታል።

የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ለምታከውናቸው ተግባራት የሚውል የበጀት ድጋፍ ነው ተብሏል።

ድጋፉ ለብሄራዊ የኮሮና ቫይረስ ዝግጁነት እና ምላሽ ማስፈፃሚያ እንደሚውል ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version