Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው።

በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ክሱ የተመሰረተው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ በተካሄደ የደን ምንጣሮ ስራ ጋር ተያይዞ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Exit mobile version