Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰሜን ኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ፣ የተወሰነ እና ሊደረስበት የሚችል አላማን ያነገበ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ፡ የተወሰነ እና ሊደረስበት የሚችል አላማን ያነገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ማክሰኞ ህወሓት ትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ መውሰድ መጀመሩን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡
እየተካሄደ ያለው ዘመቻም በሃገሪቱ ህግና ስርአትን ለማስፈን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለማስከበር ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ ተንቀሳቅሰው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
መንግስት ከህወሓት ጋር ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለወራት ታግሶ ድርድርና ሽምግልና ሲያካሂድ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጅ መንግስት ያደረገው ጥረት በሙሉ በህወሃት እምቢተኝነት መክሸፉንም ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version