Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሜ/ጀ መሀመድ ተሰማ፣ ሠራዊቱ ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያጠናቅቃል አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ፣ ሠራዊታችን ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታወቁ።
 
የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች የህዳሴ ግድባችንን እንዳያደናቅፉ የሀገራችን የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት ባሁኑ ሰዓት፣ የናት ጡት ነካሾች ሀገራችንን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ ።
 
ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ፅንፈኛው ኃይል የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት መሆኑንም ተናግረዋል።
 
በአሁኑ ሰዓት ይህንን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ኃይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ እንደሚገኙ ነው ያስረዱት።
 
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከዳር ተነሳስቶ የተከፈተብንን ጦርነት ለመመከት ተሳትፎውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ይገኛል ብለዋል።
 
ሠራዊታችን ፅንፈኛውን ኃይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ እንደሚወጣ ዋና ዳይሬክቱ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Exit mobile version