Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል።
ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያካሂድ ነው ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ያስታወቀው።
በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ነው የተባለው።
የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
Exit mobile version