Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአብዬ ደቡባዊ ሴክተር በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ የተሰማራው የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የጁንታውን ድርጊት አወገዙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአብዬ ደቡባዊ ሴክተር በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ የተሰማራው የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የህውሓት ጁንታውን ድርጊት አወገዙ ።
የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል መብረሀቶም ሀይሉ ÷ ከሀዲው የህውሀት ቡድን በሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ የፈፀመው ዘግናኝና ድርጊት ሊወገዝ ይገባዋል ብለዋል ።
በቀጣይም የተጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር በመደገፍና ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር ግዳጃችንን ያለምንም መደናገጥ አጠናክረን እናስቀጥላለን ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version