Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህግ የማስከበሩ ምዕራፍ በድል ተጠናቋል በመጭው ጊዜ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀን አንዘናጋ -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

“ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ የመከላከያ ሀይላችን ላጎናጸፈን ክብር መላው ኢትዮጵያውያንን እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል፡፡

“ህግ የማስከበሩ ምዕራፍ በድል ተጠናቋል፤ በመጭው ጊዜ ደግሞ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀን ለአፍታም አንዘናጋ” ነው ያሉት፡፡

እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ጠንክረን እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአሁኑ የመከላከያ ሃይል ድል ለዚህ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው፡፡ አኩርታችሁናልም ብለዋል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፡፡

Exit mobile version