Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች 390 ሚሊየን ብር ገቢ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ባለሀብቶች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 390 ሚሊየን ብር ገቢ አደረጉ።

በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነት ለገበታ ለሀገር ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመርሃ ግሩ ላይ የተለያዩ ባለሀብቶች 320 ሚሊየን ብር ለገበታ ለሀገር ገቢ ሲያደርጉ ቀሪውን 70 ሚሊየን ብር ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ገቢ አድርጓል።

ቃል ተገብቶ ገቢ ያልሆኑ ገንዘቦች እስከ አርብ ድረስ ገቢ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በአላዛር ታደለ

Exit mobile version