Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን ታጠናክራለች – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን እንደምታጠናክር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ እሴቶችን በመጨመር በየአካባቢው የሚገኙ ባህላዊ ማዕድን አውጪዎችን እና ማኅበረሰቦችን ሕይወት ማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ የተፈጥሮ ማዕድን የታደለች ሃገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ወርቅ፣ ቤዝ ብረቶች፣ ፖታሽ፣ ታንታለም፣ ሰንፔር፣ ኤመራልድ እና ኦፓልም በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅምን በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅም ይጠናከራልም ነው ያሉት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version