Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም ከኳታር አቻቸው ጋር ተወያዩ

Image processed by CodeCarvings Piczard ### FREE Community Edition ### on 2020-01-06 19:52:06Z | |

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ከኳታር አቻቸው ሌተናል ጀኔራል ጋህነም ቢን ሻሂን አል ጋህኒም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን ወታደራዊ ግንኙነት የጋራ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

በኳታር ዶሃ በተካሄደው በዚህ ውይይት ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተሳትፈዋል።

Exit mobile version