Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለሀገር’ መርሐ ግብር የሶስቱን መዳረሻዎች መገለጫ በኤግዚቢሽን መልክ እንዲቀርብ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ፤ወንጪ እና ኮይሻ መዳረሻዎችን መገለጫ በኤግዚቢሽን መልክ እንዲቀርብ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለረዥም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ በነበረውና ዛሬ በሚካሄደው የ’ገበታ ለሀገር’ መርሐ ግብር የሦስቱን መዳረሻዎች መገለጫ በኤግዚቢሽን መልክ እንዲቀርብ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁትን ሁሉ አመሰግናለሁ ብለዋል።
ብዝኃነታችን፣ ባህሎቻችን፣ ታሪካዊ ቅርሶቻችን እና የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ወደ ብልጽግና የመስፈንጠሪያ ልዩ አቅም ይዘዋል ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version