አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን በሕክምና ሙያ፣ በሀገር ሽማግሌነት፣ በዕርዳታ አስተባባሪነት እና በዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ሀገራቸውን ያገለገሉ ነበሩ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን በማረፋቸውን የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መጽናናትንም ተመኝተዋል ።
የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ በኮቪድ -19 ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!