Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ አሜሪካ አቀኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ አሜሪካ  አቀኑ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያቀኑት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዋሽንግተን ከተማ በሚያካሂዱት ውይይት ላይ ለመሳተፍ ነው።

ከዚህ ቀደም ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው በአውሮፓውያኑ ጥር 13 ቀን 2020  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ውይይቱን የሚያደርጉት።

በውይይቱም ሀገራቱ በተለያዩ ዙሮች የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያደረጓቸውን ድርድሮች ውጤት ይመለከታሉ።

በዚህ ውይይታቸውም አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በታዛቢነት ይሳተፋሉ።

Exit mobile version