አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክትር ሊያ ታደሰ በዓለም አቀፉ ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ ለሚያደርገው /ጂኤፍኤፍ/ ለተሰኘው ተቋም ተባባሪ ሊቀመንበር በመሆን ተሾሙ፡፡
ጂኤፍኤፍ በዓለም ባንክ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በሴቶች፣ በህጻናት እና በወጣቶች ላይ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡
በፈረንጆቹ 2015 የተቋቋመው ይህ ተቋም 36 የሚደርሱ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራትን ይደግፋል፡፡
ዶክተር ሊያ በተቋሙ ውስጥ በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላሉ መባሉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!