Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕከት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል።

ተናጠል ሳይሆን ሕብረት ዓላማን ያሳካል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ  የእግር ኳስ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማጣሪያን በማለፉ እጅግ ደስ ብሎናል፣ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

ውጤቱ እንደታወቀ በመዲናችን የመኪና ጥሩምባ እየተስተጋባ ነው፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቡድናችን ጋር ነው::ተናጠል ሳይሆን ሕብረት ዓላማን ያሳካል በርቱ ሲሉ የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version