Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በቅርቡ ተከስተው የነበሩ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት ነው ዛሬ ስምምነት ላይ የደረሱት፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌያት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት መስማማታቸውንም ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version