Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የዩኔስኮ የኮሚቴ 1970 ስምምነት አባል ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (የዩኔስኮ) የ1970 ስምምነት ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች።
ምርጫው የተካሄደው የስምምነቱ አባል ሃገራት ባካሄዱት ስድስኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።
ኮሚቴው ባህላዊ ቅርሶች በህገወጥ መንገድ ከሃገር እንዳወጡና እንዳይገቡ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ የሚከላከል እና የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ነው።
በዩኔስኮ የኢትየጵያ ቋሚ ተጠሪ የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በሃገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ሥራ ሲሰራ በመሆኑ ኢትዮጵያም የባህላዊ ቅርስ ጥበቃ ለማድረግ የበኩሏን ሚና እንደምትጫወት ገልጿል።
አያይዞም በድጋሚ እና አዲስ ለተመረጡ አባል ሃገራት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፎ፥ ኢትዮጵያ በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ መወጣቷን እንደምትቀጥል ማረጋገጧን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version