Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ ሚ ዐቢይ ሰኔ 14 ቀን ህብረተሰቡ ድምፁን ለመስጠት በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኔ 14 ቀን ህብረተሰቡ ድምፁን ለመስጠት በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ አቀርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ÷”ሰኔ 14፣ 2013 ሁለት ነገር እንትከል፤ በካርዳችን ዴሞክራሲን፣ በእጃችን ችግኞችን። ድምጻችንን ለመስጠት ሰኔ 14 ቀን በነቂስ እንውጣ”ብለዋል።
“አረንጓዴ ዐሻራችንን በማሳረፍ፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ የሚደረገውን ጥረት እንቀላቀል” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ይህን ለማካካስ ከምርጫው ቀጥሎ የሚመጣው ቅዳሜ የሥራ ቀን እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version