Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ የመጨረሻ የስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ የመጨረሻ የስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት በሱዳን ካርቱም ውይይት ጀምረዋል።

የሶስቱ ሃገራት የቴክኒክ እና የህግ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ባለው ውይይት በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የመጨረሻ የስምምነት ረቂቅ እንደሚያዘጋጁ ይጠበቃል።

በውይይቱ ላይ የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

ውይይቱ ባሳለፍነው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የሶስቱም ሃገራት የህግ ባለሙያዎች የተወከሉበት ቡድን በህግ ማዕቀፎቹ ላይ የጋራ ምክክር እንዲካሄድ መስማማቱን ተከትሎ ነው እየተካሄደ ያለው።

Exit mobile version