Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅማ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጅማ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአዌቱ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ፕሮጀክቶችን ያስመርቃሉ።

በተጨማሪም በጅማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ለብልፅግና ፓርቲ በሚደረገው የድጋፍ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ለህዝቡ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

በሙክታር ጠሃና ተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version