Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ በርበራ ከተማ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊ ሞገስና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ያካተተ ከፍተኛ ልዑክ በርበራ ሶማሌላንድ ገባ።
ልዑኩ በርበራ ሲደርስ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ልዑኩ ዛሬ የሚመረቀው የበርበራ ኮሪደር ወደብ ስነስርዓት ላይ እንደሚሳተፍ ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version