Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፈው ዓመት በርካታ የስኬት ምዕራፎችን አከናውነናል-ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት በርካታ የስኬት ምዕራፎች መከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰሩት ፅሁፍ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር የነበረው የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የክንውን ግምገማ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
ባለፈው ዓመትም በርካታ የስኬት ምዕራፎች መከናወናቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን እምቅ ዐቅም በሙሉ ለመጠቀም ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የክንውን ግምገማው መጠናቀቁን ተከትሎ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር አረንጓዴ አሻራ ማሳረፋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version