Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጁንታውን ሀይል በሚገባው ቋንቋ ለማናገር ተዘጋጅተናል – የደቡብ ወሎ ዞን ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን ወጣቶች ህዝብን ሊበላና ሀገርን ሊያፈርስ የመጣውን የጁንታ ሀይል በሚገባው ቋንቋ ለማናገር ወደ መከላከያ መቀላቀላቸውን ተናገሩ።
በርካታ ቁጥር ያላቸው የደቡብ ወሎ ዞን ወጣቶች መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀላል ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
ወጣቶቹ÷ ህዝብን ሊያባላና ሀገርን ሊያፈርስ ለመጣ የጁንታ ኃይል በሚገባው ቋንቋ ለማናገር ወደ መከላከያ ሰራዊት ተቀላቅለናል ብለዋል።
ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሠለፍ ሀገራችንን ከውጭና ከውስጥ ጠላት ለመከላከል ቁርጠኛ ነንም ነው ያሉት፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በከድር መሀመድ እና በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version