Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ እየተደረገ ያለው ድርድር ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ምክክር ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

የጭው ጉዳይ ሚኒስትሩ የናይል ወንዝ የሃገራቱን ህዝቦች ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የትብብር መነሻ ሊሆን ይገባል የሚል እምነት እንዳላቸው በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብፅን በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ አደረገች

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version