Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጥሪ አቀረቡ ፡፡
 
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች እየተደረጉ በሚገኙ የሰብዓዊ እርዳታዎች ዙሪያ መምከራቸውን አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
በተመድ የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ÷የመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Exit mobile version