Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካ ንግድ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ጋር መምከራቸውን አንስተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
Exit mobile version