Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ ቀጠናዊ የሠራተኛ አስተዳደር ማዕከል ጉባዔ የአባል ሀገራቱ ሚኒስትሮች በተገኙበት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 49ኛው የአፍሪካ ቀጠናዊ የሠራተኛ አስተዳደር ማዕከል ጉባዔ የአባል ሀገራቱ ሚኒስትሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ በይፋ ተከፍቷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ አሰግድ ጌታቸው÷የኢትዮጵያ መንግስት የሠራተኛ አስተዳደር ሀገራዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት መሰረታዊ መሆኑን ይገነዘባል ብለዋል፡፡

ማዕከሉ አፍሪካውያን የጋራ የሆኑ የሠራተኛ አስተዳደር ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version