Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የመቻልን ብቸኛ ግብ የአማካይ ተጫዋቹ ከነዓን ማርክነህ 62ኛው ደቂቃ ላይ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ይህን ተከትሎም የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈተን አስተናግዷል።

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

Exit mobile version