Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ታዬ በኢትዮጵያ የዮርዳኖስ እና ኩዌት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

Copy of Copy of በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞች ከመስከረም 1 ቀን ጀምሮ በጡረታ ዐቅድ ይካተታሉ ተባለ - 2

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የዮርዳኖስ እና የኩዌት አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ ÷ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በተለይም በኢትዮጵያና ዮርዳኖስ መካከል የተፈረመው የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁን አንስተዋል።

መሰል ስምምነቶች ኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደ ድልድይ ሊያገለግሉ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

የኩዌት አምባሳደር በበኩላቸው÷ በቅርቡ የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version