አምባሳደር ታዬ በኢትዮጵያ የዮርዳኖስ እና ኩዌት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የዮርዳኖስ እና የኩዌት አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ÷ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በተለይም በኢትዮጵያና ዮርዳኖስ መካከል የተፈረመው የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁን አንስተዋል።
መሰል ስምምነቶች ኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደ ድልድይ ሊያገለግሉ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
የኩዌት አምባሳደር በበኩላቸው÷ በቅርቡ የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።