Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች በ10 እጥፍ መጨመሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አንድ ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ መጨመሩን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አስታውቋል።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ በ10 እጥፍ እንደጨመረ ነው የታወቀው።

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ግምት ወስጥ በማስገባት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ተብሏል።

ኢንስቲትዩቱ መከላከል ከመታከም ይበልጣል፣ ቤት መቆየት ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል፣ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል ሲል ህብረተሰቡ ጥናቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

Exit mobile version