Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቀን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን የሚያመርት ፋብሪካ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ24 ሰአት ውስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ደረጃውን የጠበቀ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን ማምረት የሚችል ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ።

ጉያ ሜዲካል ማስክ ማምረቻ የተሰኘው ፋብሪካ ለ450 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል።

በዚሁ የምረቃ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ማምረቻዎች እጅግ አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።

የፋብሪካው ባለቤት አቶ ሙባረክ ከሚል በበኩላቸው የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ስራ የማስገባት እቅድ እንደነበራቸው ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጅ ኮቪድ19 አሁን ላይ በሀገሪቱ ስጋት መሆኑን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚያስችሉ ምርቶች ላይ ለመሳተፍ መወሰናቸውን ገልፀዋል።

በአክሱማዊት ገብረህይወት

Exit mobile version