Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተካሄደ።
በስብሰባው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከውጪ ንግድ የተገኘውን ገቢ፣ የዋጋ ግሽበት እና ተያያዥ እርምጃዎች፣ የመንግሥት ገቢ እና የሥራ ክንውን ሁኔታ መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
እንዲሁም ለተያዘው ዓመት በተለዩ ዐበይት ቀዳሚ ጉዳዮች መሠረት፤ ኮሚቴው ለቀጣይ ሩብ ዓመት የሚሆኑ ግቦችን ለይቶ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
Exit mobile version