Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ አቅርበዋል-ቦርዱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡
በመግለጫቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ የመጨረሻ ውጤትን ሊያዘገየው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የገለፁ ሲሆን ፓርቲዎቹ በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረው፡፡
ቦርዱም ቅሬታዎቹ በፍጥነት መፍታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በማጣራት ሂደቱም የምርጫውን ውጤት ሊለውጡ የሚችሉ ቅሬታዎች ካሉ በድጋሚ ምርጫ የምናካሂድባቸው ክልሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በህጉ መሰረት እናውቃለን ነው ያሉት ሰብሳቢዋ፡፡
በሌላ በኩልም 942 የምርጫ ውጤት ሰነዶችን ቦርዱ እያረጋገጠ ለህዝቡ እንደሚያቀርብ ገልፀዋል፡፡
እስካሁንም 618 የሚሆኑ የምርጫ ውጤት ሰነዶች ወደ ማዕከል መጥተዋል ነው ያሉት፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version