Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የእስካሁን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተከትሎ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ላይ የሚኒስትሮች ኮሚቴ፣ ከፓርላማ መርማሪ ቦርድ አባላት እና ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን አስታወቁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፓርላማ መርማሪ ቦርድ አባላት እና ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይት ፍሬያማ መሆኑንም በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ማህበረሰቡን ከወረርሽኙ በመታደግ፤ ሃገሪቱን በማሻገር ሰልፍ ውስጥ ዜጎችን ማዕከል ባደረገ እንቅስቃሴ ተቀራርቦ እና ተደጋግፎ ለጋራ ውጤት መስራት የሚያስችል ውይይት መሆኑንም አንስተዋል።

እንዲሁም በውይይቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ሂደት በእስካሁን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ መልካም ጅምሮችን በማጠናከር፣ በህግ ማዕቀፍ አወጣጥ ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን በማረም፣በተግባር እንቅስቃሴ ከሚታዩ ውስንነቶች ትምህርት በመውሰድ እንዲሁም ከወረርሽኙ ባህሪ በመነሳት ከህጉ አንፃር በቂ ዝግጅት እና ተመጣጣኝ ምላሽ በመስጠት በሚያስችል አግባብ ገንቢ ምክረ ሃሳቦች ተለዋውጠናል ብለዋል።

Exit mobile version