Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ 165 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ወደ ውጭ መላኩን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፈው በጀት ዓመት 165 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ወደ ውጭ መላኩን አስታወቀ።

አፈጻፀሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ54 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ልዩነት እንዳለው ተገልጿል።

ባለሀብቶች በአንድ ማዕከል ሁሉንም አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

በኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግና ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ደርቤ ደበሌ ÷በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረቡት ምርቶች ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት።

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ብረታ ብረት፣ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችና የግብርና ውጤቶች በመላክ ከተገኘው ገቢ ከዕቅዱ 73 በመቶ መሳካቱን አስታውቀዋል።

ምርቶቹም በዋነኝነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች መላካቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.