Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሳሙኤል በአንድ ማይል የ2020ን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በአንድ ማይል ርቀር ሩጫ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ።

በትናንትናው ዕለት በአየርላንድ አትሎን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ተካሂዷል።

አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ውድድሩን አሸንፏል።

በዚህም በፈረንጆቹ 2020 በአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል።

ስኮትላንዳዊው ስኮት ኦሃር ርቀቱን በ3 ደቂቃ 55 ሰከንድ ከ61 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ የወቅቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነው።

ምንጭ፦ African Athletics United

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.