Fana: At a Speed of Life!

746 ሺህ ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ በተከሰተ ሁከት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የራቁ 746 ሺህ ህጻናትን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።

መርሃ ግብሩ ኢዱኬሽን ካን ኖት ወይት በሚባል ድርጅት ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ በ728 ትምህርት ቤቶች በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ከትምህርት ገበታቸው የራቁ ተማሪዎችን ያካትታል።

በትምህርት ሚኒስቴር የበላይነት የሚመራው ይህ መርሀ ግብር በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በ44 ወረዳዎች የሚተገበር ይሆናል ተብሏል።

ለመርሃ ግብሩም 165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 27 ሚሊየን ዶላሩ መለቀቁ ተገልጿል።

ቀሪው 138 ሚሊየን ዶላር በሶስት ዓመታት ውስጥ የሚለቀቅ ሲሆን፥ ተጠቃሚ ከሚሆኑት 746 ሺህ ህጻናት ውስጥ 365 ሺህ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ጺዮን ተክሉ፥ በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ሁከቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ህጻናት የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የኢዱኬሽን ካን ኖት ወይት ዳይሬክተር ያስሚን ሸሪፍ በበኩላቸው፥ መርሃ ግብሩ በጥቃት፣ በድርቅ፣ በመፈናቀልና በሌሎች ሁከቶች የተጎዱ ህጻናትን ተጠቃሚ ያደርጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.