Fana: At a Speed of Life!

አርሶ አደሩ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የመጠቀም ልምዱን ሊያሳድግ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ አደሩ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የመጠቀም ልምዱን ሊያሳድግ እንደሚገባ የፌዴራል የህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ።

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በቦቆጂ ከተማ የአርሶ አደሮች ፌስቲቫል ተከፍቷል።

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት ዋና ዳይሬክተሩ የአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ እንዲሻሻል መሰል ፌስቲቫሎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

የአርሶ አደሮች ፌስቲቫል ልምድ ከማስፍት ባሻገር የቴክኖሎጂ ልምምዱን ለማሳደግ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።

መንግስት የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዘመናዊ አሰራሮችን መተግበር የሚያስችሉ መመሪያዎችን ማሻሻሉን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ከታክስ ነፃ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎች ማስገባት እንዲቻል ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን አሰራር አርሶ አደሩ መጠቀም አለበት ብለዋል።

በቦቆጂ ከተማና አካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች እየተሳተፍበት በሚገኘው ፌስቲቫል ለግብርና ዘርፍ ግብአት የሆኑ ዘመናዊ መሳሪያዎች ቀርበዋል ።

ይህም አርሶ አደሩ ልምድ እንዲያገኝ ያስችላል የተባለ ሲሆን የአርሲ ዞን በሰብል ምርታማነቱ ይታወቃል ።

በሀይለየሱሰ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.