Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 4 ሺህ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ12 ሺህ 951 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሺህ 11 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 12 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።
እንዲሁም 844 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው ያሉት።
366 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.