Fana: At a Speed of Life!

የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል  ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡

ከሁለት ወራት በኃላ ለሚጀመረው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዉን ያለፉ ሀገራት የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል::

በዚህም በምድብ አንድ ካሜሮን፣  ማሊ፣ቡሪኪና ፋሶ እና ዚምባቡዌ ሲደለደሉ በምድብ ሁለት ሊቢያ ፣ዲሚክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ኮንጎ እና ኒጀር ተደልድለዋል፡፡

እንዲሁም በምድብ ሶስት ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ቶጎ ተገናኝተዋል።

በምድብ አራት ደግሞ ዛምቢያ፣ጊኒ፣ናሚቢያ እና ታንዛኒያ መደልደላቸው ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ውድድር መድረክ በዋና ዳኝነት ጨዋታውን ከሚመሩት 20 የመሀል ዳኞች አንዷ ሆና መመረጧን ከኢትዮ ኪክ ኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.