Fana: At a Speed of Life!

አፕል የኮሮና ቫይረስ የአይፎን አቅርቦትን ሊጎዳ እንደሚችል አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አፕል ከኮሮቫ ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በቻይና ከተፈጠረው አለመረጋጋት  የአይፎን አቅርቦት ሊጎዳ እንደሚችል  አስጠነቀቀ፡፡

በቻይና ገቢን ሊያሳጡ የሚችሉ  ሁኔታዎች እንዳሉ የሚያሳዩ ትንበያዎች  መኖራቸውን ግዙፍ የቴክኖሎጂ  ኩባንያ ገልጿል፡፡

በቻይና ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ መደብሮች ተዘግተው የሚቆዩ ወይም በተወሰኑ  ሰዓቶች ብቻ ክፍት ሆነው  የሚሰሩ በመሆኑ የአፕል ምርቶች ሽያጮች ዝቅ ማለቱንም ነው ኩባንያው አመላክቷል፡፡

ኩባንያው ምርቶቹ እና ሽያጮቹ ላይ ችግር እየደረሰ በመሆኑ በዓለም ዙሪያ የአይፎን አቅርቦት ለጊዜው እንደሚገደብ ነው የጠቆመው፡፡

አፕል በወረርሽኙ ምክንያት  ገቢው ሊጎዳ እንደሚችል  ይፋ ያደረገ የመጀመሪያው ግዙፍ የአሜሪካ ኩባንያ ያደርገዋልም ተብሏል።

በተያዘው ሩብ ዓመት 67 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ገቢን ያገኛል ተብሎ የሚጠበቀው አፕል ፣  በወረርሽኙ ምክንያት ምን ያህል የገንዘብ ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል  አልገለፀም።

በቻይና  የሚገኙት ሁሉም መደብሮቻችን እንዲሁም የአጋር ሱቆቻችን  አብዛኛው የተዘጉ ሲሆን÷ ክፍት የሆኑትም ብዙ ደንበኞች በሌሉት ለትንሽ ሰዓታት እየሰሩ መሆናቸውን ኩባንያው ገልጿል።

ቀስ በቀስ የችርቻሮ መደብሮችን በመክፈት  በተቻለ መጠን ስራውን ጥሩ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀስ ኩባንያው አስታውቋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.