Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ከመገናኛ ብዙሃን እና ከባለሙያዎች ብዙ ይጠበቃል – ምሁራን

አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ከመገናኛ ብዙሃን እና ከባለሞያዎች ብዙ እንደሚጠበቅ ምሁራን ገለጹ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር አደም ጫኔ እና የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጉዳይ ተመራማሪው በቀለ ሀብታሙ÷ መገናኛ ብዙሃን ሂደቶቹን ከወዲሁ እየተከታተሉ ዜጎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው አካሄዱም ሁሉን አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ መቻል አለባቸው ብለዋል።

የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት የሚያጎሉ ሀሳቦች በሁሉም የክርክር እና የውይይት መድረኮች መንፀባረቅ አለባቸው ሲሉም ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ወሳኝ ጉዳዮችን በአማከለ መልኩ አካታች እና አሳታፊ ሆኖ ሊካሄድ እንደሚገባም ነው ምሁራኑ ያሳሰቡት።

ሂደቱም የሁሉንም ፍላጎቶች በሚያንጸባርቅ፥ ብሄራዊ ጥቅምን እና የህዝቦችን አንድነት በማይጎዳ መልኩ ሊከናወን ግድ ይላል ነው ያሉት ምሁራኑ።

በአፈወርቅ አለሙ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.