Fana: At a Speed of Life!

”እኔ ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”እኔ ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
 
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩን ያዘጋጀው ኢትዮ- ጀርመን ለኢትዮጵያ ኮሚቴ ሲሆን፥ በዝግጅቱ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲያስፖራዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይም እያንዳንዱ ዲያስፖራ 12 ሺህ ብር በመክፈል የሚታደም ሲሆን ገቢውም ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ይውላል ተብሏል፡፡
 
ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚህን ወቅት መርሃግብሩን ላዘጋጀው ኢትዮ- ጀርመን ለኢትዮጵያ ኮሚቴ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን መደገፍ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.