Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ኮንፈረንስና ግንኙነት መድረክ በአፋር ክልል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ዞን 5 ሰሙ ሮቢ ወረዳና የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስና ግንኙነት መድረክ በአፋር ክልል በኮማሜ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ከግጦሽና በዕለት ግጭቶች ልዩነቶች ይስተዋሉ እንደነበር ተነስቷል።

የትህነግ ሽብር ቡድንን በጋራ ሆነው የተፋለሙት የአፋርና አማራ ህዝቦች ፥ “በጠላታችን መቃብር ላይ እኛ አንድነታችን ጠንክሯል” ሲሉ የሁለቱ ህዝብ ተወካዮች ገልጸዋል።

ይህን እንደ ብረት የጠነከረ ግንኙነት ለማስቀጠልና በሽብር ቡድኑ ላይ የተገኘውን ድል በጋራ ለማክበር ተዘጋጅተዋልም ሲሉም ነው የገለጹት።
መርሃ ግብሩ በሀይማኖት አባቶች ጸሎት ተጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ የሁለቱ ክልሎች የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የህዝብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የአፋር ክልል ሐሊ ረሱ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ማቲ እንዳሉት ፥ ሁለቱ ተጎራባች ወረዳዎች የአፋርና አማራ ህዝቦች በአንድ ግንባር የአሸባሪዎቹ የህወሃት ወራሪ ሀይልን እና ሸኔን በመፋለም በጋራ ድል አድርገዋል ።

ይህ አብሮነትና ህብረት ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል የአፋር ህዝብ አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን በመፋለም ያደረገውን ተጋድሎ ታሪክ አይረሳውም ያሉ ሲሆን ፥ የአፋር ህዝብ ከአማራ ህዝብ ጋር በጋራ ቆሞ ቡድኖቹን ድል የነሳ ነው ብለዋል።

አቶ ሲሳይ በቀወትና አንኮበር የገባውን ወራሪ ሀይል የአፋር ወንድሞቻችን አብረውን በመሠለፍ ታሪክ ሰርተዋል ብለዋል።

በግርማ ነሲቡ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.